Friday, December 6, 2013

“ታህሳስ 5 ከሰአት በኋላ ለመገደል ፈርሜአለሁ”

SOURCE: GOLGUL

(ዶ/ር ካሳሁን በጋሻው)euthanasia

ታህሳስ 5 ከሰአት በኋላ ለመገደል ፈርሜአለሁ ገጽ 410 ይላል የስደተኛው ማስታወሻ፤ አቶ ተስፋዬ ገብረአብ “ጓደኛዬ” የሚለው ሆላንዳዊ ስለያዘው የሞት ቀጠሮ ሲያብራራ፤-
ለሚቀጥለው … ማስታዉሻ መጽሀፉ ይረዳው ዘንድ ሆላንድ ውስጥ የሞት ቀጠሮ እንዴት እንደሚያዝ ከዚህ በታች አብራራለሁ፤ ከዚያ በፊት ግን ስለ ስደተኛው ማስታወሻ የምለው ከዚህ የሚከተለውን ነው፤ ጫልቱ ብሎ የሰየማትን ተዋናይ እዛው የቡርቃ ዝማታው ላይ ቢከታት ኖር ገጸ ባህርይዋ ከዛ ጋር ይሰምርለት ነበር፡፡ ነገር ግን ከአለቆቹ የደረሰው ትእዛዝ አማራና ኦሮሞን ማፋጀት የኢትዮጵያን ስማ ማጥፋት በመሆኑ የግድ መካተት ነበረባት፤ በጎሳ እምነት የተለከፉ ሰዎች አመለካከታቸው ወደሌላ ሰውነት እንደተሰራጨ ካንሰር ነው፤ ቢነግሩአቸው ቢያስረዷቸው አይጠሩም፤ የተስፋዬ ገብረአብ ተማሪዎች በቀደም ሳውዲ አረቢያን ተቃውሞ ሰልፍ ላይ በእንግሊዝኛ  “እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ሳውድ አረቢያ ሴቶቻችንን መድፈር አቁሚ፤ ወንዶቹን መግረፍ አቁሚ” እያሉ መፈክር ይዘው ሳይ ምን ያህል እንደዘቀጥን እነ ተስፋዬም የደከሙበት ፍሬ ማፍራቱን ሳይ አዘንኩ፤ ምን ለማለት ፈልገው እንደሆነም ግልጽ አይደለም “ኢትዮጵያውያንን አሰቃዩ እኛን ደርባቹህ የምታሰቃዩን ኢትዮጵያዊ መስለናችሁ ነው ለማለት ነው?” ማንስ ቢሆን ለምን ይሰቃያል? ተስፋዬና አለቆቹ ግዜው ሲደርስ በዘር ማጥፋት ወንጀል ለፍርድ ሊቀርቡ የሚገባቸው ሰዎች ናቸው፤
ወደ ተነሳሁበት ልመለስና ለመግደል የሚፈረመው እንዴት ነው? ተስፋዬና አለቆቹ የሚቃወማቸውን ሁሉ ያለተከላካይ ስለሚያጠፉ የሰው ሕይወት ዋጋ ግንዛቤውም ስለሌላቸው ሌላውም አገር እንዲሁ ይመስላቸዋል፤ “ዐይን አላቸው አያዩም ጆሮ አላቸው አይሰሙም”
በሕክምና በሕጋዊ መንገድ መሞት፤
ይህ ድርጊት በአብዛኛው አገሮች እንደ ወንጀል የሚታይ ሆላንድ ውስጥ ግን በሕጋዊ መንገድ የሚካሄድ አሰራር ነው፤ በጣም ከባድና አነጋጋሪም ነው፤ እኛ ማነንና ነው የሰው ሕይወት የምናጠፋው ወይም ለመሞት ፈቃድ የምንሰጠው? በሽተኛው መረዳት ካልተቻለና ብዙ የሚሰቃይ ከሆነ ከስቃዩ ማላቀቅ ወንጀል ነው ወይ? እራሱን የቻለ ከሁለት ክፉ ምርጫዎች (dilemma) አንዱን መቀበል ነው። ይህ የሕክምናስ ስነምግባር (medical ethics) ነው ወይ? ሐኪም ሊያድን እንጂ ሊገል ነው ወይ የተማረው የመሳሰሉት እርስ በርስ የሚቃረኑ ሀሳቦች ጉዳዩን ያወሳስቡታል፡፡
ተስፋዬ ገብረአብ ሆን ተብሎ ጎሳዎችን ለማጋጨት በታቀደ አሰራር ውስጥ ለፖለቲካ ግብ እንዲመች እራሱን የቻለ ቅደም ተከተል ያለው ኢትዮጵያን ለማፍረስ አንድነትን ለማናጋት በሚከናወን አጀንዳ ስር ነው የተለያዩ ፍሬ ከርስኪ አጀንዳዎቹን የሚያቀርብልን። ከዚያ መሃል ግን ሃላፊነት በጎደለው መልኩ ያላየውን አየሁ ያልሰማውን ሰማሁ ብሎ ይተርካል፡፡
እኔ የዚህ ጽሁፍ ጸሐፊ የሞት ቀጠሮ ተብሎ የሰፈረው ታሪክ እንደ መጽሀፉ አብዛኛው ክፍል በጫት ምርቃና ላይ ተመርኩዞ የተደረገ እንጂ እሱ ባለው መሰረት አለመሆኑን ከዚህ በታች አስረዳለሁ፡፡
በእንደዚህ አይነት መንገድ በሐኪም እርዳት ለመሞት የፈለገ በሽተኛ በቅድሚያ በሕክምና መዳን የማይችል በሽታ እንደያዘው መረጋገጥ አለበት፤ እነዚህ በሽተኞች አብዛኞቹ የካንሰር በሽተኞች ሲሆኑ የተያዙበት ካንሰር ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨቱ ምክንያት በቀዶ ጥገና “በኪሞ ቴራፒ” በጨረር ሕክምና ሊረዳ እንደማይችል የተረጋገጠ ነው።

WATCH Bergen public meeting advertisment on 14 Dec 2013

MUST WATCH NEW MUSIC DEDICATED TO ETHIOPIAN IMMIGRANT - Shambel belayneh Wegenea teteka

Thursday, December 5, 2013

President Obama's comments about death of Mandela

President Barack Obama on Thursday mourned the death of South Africa's first black president Nelson Mandela, the anti-apartheid icon. Obama made a somber appearance at the White House to talk about the loss of Mandela with whom he shares the distinction of being his nation's first black president.

"At his trial in 1964, Nelson Mandela closed his statement from the dock saying, 'I have fought against white domination, and I have fought against black domination. I have cherished the ideal of a democratic and free society in which all persons live together in harmony and with equal opportunities. It is an ideal which I hope to live for and to achieve. But if needs be, it is an ideal for which I am prepared to die.'
"And Nelson Mandela lived for that ideal, and he made it real. He achieved more than could be expected of any man. Today, he has gone home. And we have lost one of the most influential, courageous, and profoundly good human beings that any of us will share time with on this Earth. He no longer belongs to us — he belongs to the ages.
"Through his fierce dignity and unbending will to sacrifice his own freedom for the freedom of others, Madiba transformed South Africa — and moved all of us. His journey from a prisoner to a President embodied the promise that human beings — and countries — can change for the better. His commitment to transfer power and reconcile with those who jailed him set an example that all humanity should aspire to, whether in the lives of nations or our own personal lives. And the fact that he did it all with grace and good humor, and an ability to acknowledge his own imperfections, only makes the man that much more remarkable. As he once said, 'I am not a saint, unless you think of a saint as a sinner who keeps on trying.'
"I am one of the countless millions who drew inspiration from Nelson Mandela's life. My very first political action, the first thing I ever did that involved an issue or a policy or politics, was a protest against apartheid. I studied his words and his writings. The day that he was released from prison gave me a sense of what human beings can do when they're guided by their hopes and not by their fears. And like so many around the globe, I cannot fully imagine my own life without the example that Nelson Mandela set, and so long as I live I will do what I can to learn from him.
"To Graça Machel and his family, Michelle and I extend our deepest sympathy and gratitude for sharing this extraordinary man with us. His life's work meant long days away from those who loved him the most. And I only hope that the time spent with him these last few weeks brought peace and comfort to his family.
"To the people of South Africa, we draw strength from the example of renewal, and reconciliation, and resilience that you made real. A free South Africa at peace with itself -- that's an example to the world, and that's Madiba's legacy to the nation he loved.
"We will not likely see the likes of Nelson Mandela again. So it falls to us as best we can to forward the example that he set: to make decisions guided not by hate, but by love; to never discount the difference that one person can make; to strive for a future that is worthy of his sacrifice.
"For now, let us pause and give thanks for the fact that Nelson Mandela lived — a man who took history in his hands, and bent the arc of the moral universe toward justice. May God Bless his memory and keep him in peace."

ከሳዑዲ አረቢያ ከተመለሱት ውስጥ 8 ሺህ የሚሆኑት ነብሰጡር ናቸው ተባለ | Zehabesha Amharic

ከሳውዲ ዓረቢያ ከተመለሱ ስደተኞች መካከል 8 ሺህ ሴቶች ነብሰ ጡሮች መሆናቸውን FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል በክር ዋቢ በማድረግ ዘገበ ። ከተጠቀሱት ነፍሰጡር እህቶቻችን መሃከል በሪያድ እና በጅዳ የሚገኙ የኮሚኒ ግዜያዊ መጠለያ ከገቡ በሃላ አስገድዶ መድፈር ወንጀል ሳይፈጸምባቸው እንዳልቀረ ምንጮች ገለጹ። ቀሪውን እዚህ ጋር ያንብቡ።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10470

የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡


GREAT NEWS!!
የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡
ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ)
በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ ነው፡፡
ስለቅርሱ የመረመረው ኮሚቴ ባቀረበው ውሳኔ ሐሳብ ላይ እንደተመለከተው፣ የመስቀል ክብረ በዓል የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶችን የያዘ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ መምጣቱና በአገሪቱ ማኅበራዊ አንድነትንና የርስ በርስ ትስስርን፣ ብዝኃነትንም የሚያንፀባርቅ፣ በበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች መካከል ትስስርን የፈጠረ በመሆኑ ዓለም አቀፍ መስፈርቱን አሟልቷል ብሎታል፡፡
የዩኔስኮ ኮሚቴው በረቡዕ ስብሰባ ውሎው ከመስቀል ሌላ ከተለያዩ አገሮች 13 መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶችን በሰው ዘር ቅርስነት መመዝገቡንም በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
መስቀልን ጨምሮ እ.ኤ.አ. በ2013 የተመረጡትን የ14ቱ መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶች ገጽታ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችና ፎቶዎችም በዕለቱ በድረ ገጹ ላይ መለቀቃቸው ታውቋል፡፡
በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን በመላ አገሪቱ በአደባባይ ደመራ የሚከበረው የመስቀል ክብረ በዓል የመጀመርያው መንፈሳዊ (ኢንታንጅብል) ባህላዊ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበላት ኢትዮጵያ፣ ዘጠኝ ግዙፍ (ታንጀብል) ቅርሶች ማስመዝገቧ ይታወቃል፡፡

Amnesty urges gov’t to free Eskinder Nega


December 5,2013.

Rights group launches a global appeal for the release of journalist sentenced to 18 years on terrorism charges.

(Al Jazeera) Rights group Amnesty International has issued a global appeal for the release from prison of an award-winning journalist in Ethiopia.

Amnesty on Wednesday said it was trying to raise awareness of the case of Eskinder Nega as part of a campaign called “Write for Rights.”

Eskinder, in prison since 2011, is serving an 18-year sentence on terrorism charges.

Amnesty says the journalist was a “thorn in the side of the Ethiopian authorities” for making speeches and writing articles critical of the government.

Eskinder’s wife, Serkalem Fasil, who was arrested with him but later released, and who now lives in the US, said her husband was arrested for being a journalist and for repeatedly criticising the government.

Ethiopian government spokesman, Shimelis Kemal, said Eskinder was not convicted for his criticism of the government but because he was running a clandestine ‘terrorist’ organisation.

According to the Committee to Protect Journalists, Ethiopia has the second highest number of journalists imprisoned in Africa and is the eighth biggest jailer of journalists in the world..

Tuesday, December 3, 2013

የመለስ ዜናዊ አስገራሚ ቃለ-ምልልስ ሲዳሰስ እስክንድር ነጋ

ጠ/ሚ/ሩ ቃለምልልስ እየሰጡ ነው… ቅዳሜ መጋቢት 3/2ዐዐ3 …በዚያን ሰሞን ሞላ ብሎ የነበረው ሰውነታቸው አሁን ከሳ ብሏል… ውይ! ውይ! ውይ!… እኔን! ግን… ግን… ከትላንት ወዲያ ቱኒዚያ፣ ትላንት ግብፅ፣ ዛሬ ደግሞ ሊቢያ እየተፈራረቁባቸው ከሳ ማለትማ ይነሳቸው እንዴ?… «ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል» እንጂ፣ የሰሞኑ የመለስ የስጋት ኑሮ «ውስጡን ለቄስ» እንደተባለው ነው… የስቃይ ኑሮ… አሳዛኝ ኑሮ… እኔን!
የወትሮው «መፈክር አውራጁ» መለስ ዛሬ ቀዝቀዝ ብለዋል፡፡ ስለኢኮኖሚው ተጠይቀው ሲመልሱ ሃሳባቸው ሌላ ቦታ ይመስላል፡፡ ዋናዎቹን ጥያቄዎች እየጠበቁ ይመስላሉ… የቱን ጥያቄዎች?… ከእንጥፍጣፊዎቹ በኋላ የሚመጡትን… ህዝባዊ ተቃውሞ በኢትዮጵያ ይቀሰቀሳል ብለው አልሰጉም ወይ? (ያው መስጋታቸው ቢታወቅም…) ህዝባዊ ተቃውሞ ቢነሳ፣ ሠራዊቱ እንዲተኩስ ትዕዛዝ ይሰጣሉ ወይ?… የግብፅና የቱኒዚያ ሠራዊቶች በህዝባቸው ላይ አንተኩስም ማለታቸውን እንዴት ይመለከቱታል?… ህዝባዊ ተቃውሞ ቢነሳ፣ ሥልጣንዎን በፈቃድዎ ይለቃሉ ወይ?… አውራው የዴሞክራሲ እንቅፋት መለስ ዜናዊ ናቸው የሚባለውን እንዴት ይመለከቱታል?… ኧረ ስንቱ ! ኧረ ስንቱ !… እነዚህ ጋዜጠኞች አንጀታችንን ሊያርሱት ነው… ሶፋዬ ላይ ተመቻቸኹ… ዛሬ ጉድ ሊፈላ ነው!!
እንጥፍጣፊ ጥያቄዎቹ ግዜ እየፈጁ ነው… ሃ… ሃ… ሃ… ሃ… ሃ… አዘጋኹ… አሰልቺ ጥያቄዎች፣ አሰልቺ መልሶች… በእጄ የያዝኹትን መፅሃፍ ማገላበጥ ጀመርኹ… ደቂቃዎች አለፉ…
ሴቷ ጋዜጠኛ ጀመረችው… ደስ አይልም?… ወንዶቹ ደግሞ ይቀጥላሉ… አለሳልሳ ነው ጥያቄውን ያቀረበችው… እነዚህ ጋዜጠኞች ተነጋግረው መሆን አለበት… ቀስ ብለው ጀምረው፣ ሳይታሰብ ሊያፍረጠርጡት መሆን አለበት…
«በሰሜን አፍሪካ ሕዝባዊ ተቃውሞ ያስነሱት ክስተቶች በኢትዮጵያ ውስጥም እንዳሉ ተቃዋሚዎች ይናገራሉ፡፡ በዚህ ላይ እርስዎ ምን አስተያየት አለዎት?»… አለቻቸው ጋዜጠኛዋ… በጨዋ ቋንቋ የቀረበ ቆንጆ ጥያቄ… በጨዋ ቋንቋ ለሚቀርቡ ከበድ ከበድ ለሚሉ ጥያቄዎች ጥሩ በር ከፋች….
መለስ ዜናዊ ምላሽ እየሰጧት ነው…
«እኔ ተመሳሳይ ተቃውሞ ይነሳል የሚል ግምት የለኝም…» …እያሉ ነው መለስ፤ የሚጠበቅ ነው… «ለምን ይነሳል?…» …እየተሟሟቁ ነው ጠ/ሚ/ራችን… «ህዝቡ የ5 ዓመታት ኮንትራት ከሰጠን ገና 1ዐ ወራት እንኳን በደንብ አላስቆጠሩም…» …እሺ አቶ መለስ፤ ቀስ ይበሉ…
«በድምፁ፣ በካርዱ ነው ይሄን ኮንትራት የሰጠን…» …ሳላውቀው ሶፋው ጠርዝ ላይ ደርሻለኹ፤ ምንም ነገር እንዳታመልጠኝ እየተለጠጥኹ ነው… «ለመፈፀም ቃል የገባነውን ዳር ለማድረስ ጠዋት ማታ ደፋ ቀና እያልን ባለንበት ግዜ፣ አሥር ወር ሳይሞላ በመንገድ ላይ ነውጥ ሊያስቆመን የሚወጣው ለምንድን ነው?…» …አልበቃዎትም አቶ መለስ?… «በዚያ ላይ ደግሞ…» …ቀጠሉ ጠ/ሚ/ሩ… «ኢትዮጵያ በህግና በሥርዓት፣ በሰላማዊ መንገድ መንግሥት ለመለወጥ የሚቻልበት ሀገር ናት…» …አሁን ጆሮዬን እየኮረኮርኹ ነው… የማዳምጠው በትክክል ነው?… «ከ5 ዓመታት በኋላ ህዝቡ ምርጫ ካርዱን ተጠቅሞ ኢሕአዴግን በዝረራ ከሥልጣን ሊያባርረው እንደሚችል ህዝቡ ያውቀዋል…» …አሁን ከተቀመጥኹበት ፍንጥር ብዬ ተነስቻለሁ!… ህዝቡ ያውቀዋል? ነው ያሉት?… አቤት!… አቤት!… አቤት!… አቤት አለማፈር!… «ኢሕአዴግም ያውቀዋል…» …አሉ መለስ …ባለቤቴ ሳቋን ለቀቀችው… «ይሄን እያወቀ ለምንድን ነው ወደ መንገድ ላይ ነውጥ የሚሄደው?» …እዚህ ጋር መለስ ተሽከርካሪ ወንበራቸውን ትንሽ ወደኋላ ገፋ አደረጉት… እና… እና… ሁለቱንም እጃቸውን አወናጨፉ!… ለካ በስሜት ከንፈዋል… አይ መለስ!
ቃለ-ምልልሱ አበቃ… ጠ/ሚ/ሩ ተነስተው ወጡ…
ታዲያ፣ ለዚህ ምን ምላሽ ነው የሚሰጠው? የት ነው የሚጀመረው? ወደ ሰኔ 1983 እንመለስ? ሁለት አስርት ዓመታት ወደኋላ ተጉዘን፣ ሰፊ ህዝባዊ መሠረት በነበረው ኢዴኃቅ ላይ የሽግግር መንግሥቱ አካል አንዳይሆን በር በመዝጋት የተጀመረው ኢ-ዴሞክሲያዊነት፣ ዘንድሮ ወደ ተዘመገበው 99.6% «የምርጫ ድል» እንዴት እንዳደገ እንዘክር? «ዝክረ ኢ-ዲሞክራሲ ወኢሕአዴግ» ልንለው እንችላለን፡፡ አንድ ትልቅ መፅሃፍ ይወጣዋል፡፡
እዚህ ውስጥ መነከር ግን፣ ወይ የጠ/ሚ/ሩን አባባል እውነት ነው ብሎ የሚያስብ አንድ ሰው ሊኖር ይችላል ብሎ መጠራጠርን ይጠይቃል፣ ወይ ደግሞ፣ ሌላ የሚፃፍለት ቁምነገር ጠፍቶ፣ አንድ ሺህ ግዜ ስለተፃፈለት እውነታ ለአንድ ሺህ አንደኛ ግዜ መፃፍ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ፣ መለዕኮታዊ ትዕግሥትና የተትረፈረፈ ግዜ ያስፈልገዋል፡፡ በእኔ በኩል ሁለቱም የለኝም፡፡
ስለዚህ፣ በአዲሱ ሚሊኒየም በአስገራሚነቱ ቀዳሚ ስፍራ የያዘውን ምላሻቸውን በትዝብትነቱ ብቻ በማስቀመጥ አልፌዋለኹ፡፡
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ትንሽ ሳልዳስሰው የማላልፈው ጉዳይ ግን አለ፡፡ ከመለስ አስገራሚ «ትንታኔ» ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ሰፊ ባሕር ነው፤ በጥልቀት ልሄድበት አልከጅልም፡፡
ቅድመ 66 አብዮት፣ የቤተመንግሥት ስርዓት ነበር፡፡ ይህ ሰፊ አድማስ ያለው ወግ፣ በተራዘመ አዝጋሚ የለውጥ ሂደት (ፈረንጆቹ Evolutionary የሚሉት) ዳብሯል፡፡ ርዕሰ ብሔርነቱንና መንግሥትነቱን አቀናጅተው ለሺህ ዓመታት የዘለቁት የኢትዮጵያ ነገስታትና መኳንቶቻቸው ከአቋቋም፣ ከአቀማመጥ፣ ከአነጋገር፣ ከአለባበስና ከአበላል አንስቶ እስከ ኃይማኖት፣ ግልቢያ፣ ውጊያና ፍርድ አሰጣጥ ድረስ ተምረዋል፡፡ ታላላቆቹ ነገሥታት በአንዱ ወይም በሌላው የላቀ ብቃት አስመዝግበዋል፡፡ ብዙዎቹ በመንፈሳዊነታቸውና በተዋጊነታቸው ልቀው ወጥተዋል፡፡ የአንዳንዶቹ የገዘፈ ክህሎት በታሪክ ማሕደር ላይ ጎላ ብሎ ሰፍሯል – - – አፄ ዘርያዕቆብ በመንፈሳዊነታቸው፣ አፄ አምደፅዮን በወታደራዊ አመራር ሰጪነታቸው ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
ነገሥታቱ ሀገር ከመጠበቅና ከመምራት ባሻገር፣ ለሚመሩት ሕዝብ አርአያ ሆኖ መመሰል ይጠበቅባቸዋል፡፡ አበላላቸው፣ አቀማመጣቸው፣ አነጋገራቸው ወዘተ… ጭንቅ ውስጥ የገባው በዚህ ታሳቢ ነበር፡፡
ይህ ግን ለመለስ ዜናዊ ቦታ እንደሌለው ትላንት አብስረውልናል፡፡ «በጠ/ሚ/ርነቴ ኮንትራት የገባሁት ለ8 ሰዓታት ስራ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪRole Model (አርአያ) ለመሆን የገባሁት ውል የለም፡፡ የታመመን በመጠየቅ፣ ትምህርት ቤት በመመረቅ አላምንም» ብለው እቅጩን ነግረውናል፡፡ (ቀጥተኛ ጥቅስ ነው፡፡)
በመለስ ቀመር፣ ከአነጋገራቸው ጋር «ኮንትራት» የለንም፡፡ የእኛ «ኮንትራት» ኢኮኖሚው በምን ያህል አደገ? የዋጋ ግሽበቱ በቁጥጥር ስር ውሏል ወይ? የውጭ ንግድና የመንግሥት ባጀት ጉድለቶች ምን ደረጃ ላይ ናቸው? በሚሉትና በመሳሰሉት ጥያቄዎች ዙሪያ ብቻ የታጠረ ነው፡፡
ስለዚህም፣ መለስ ዜናዊ እንዳመጣላቸው እየተናገሩ ይኸው ሃያ ዓመታትን አብረን አዝግመናል፡፡ በዘፈቀደ የሚወረውሯቸውን ቃላትና አባባሎች እያደመጠ የተኮተኮተ፣ ያደገና ለአቅመአዳም የደረሰ አንድ ትውልድ በቅሏል ማለት ነው፡፡
ይህ ትውልድ ለእውነትና ለጨዋነት ምን ያህል ዋጋ ይሰጣል? የሚለው ጥያቄ ሁልጊዜ ያሳስበኛል፡፡ መለስ ዜናዊ ተገነዘቡትም አልተገነዘቡትም፣ መሪዎች በሁሉም ሀገራት ትልቁን የአርአያነት ሚና ይጫወታሉ፤ በጥንቷ ኢትዮጵያ ብቻ አይደለም፡፡ አሜሪካዊያን፣ ፕሬዝዳንቶቻቸው ስለትናንሽ የግል ሕይወታቸው ሳይቀር እውነት መናገራቸውና አለመናገራቸው ከልብ የሚያስጨንቃቸው ተቀናጥተው አይደለም፡፡ ለውሸቱ ዋጋ የማይከፍል መሪ፣ መዋሸትን እንደ ነውር የማይቆጥር ትውልድ ያፈራል ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡ የእነሱ ስጋት በሀገሬ እውን ሆኖ እንዳላይ የምር እፈራለሁ፤ እድሜ ለመለስ፡፡
ከዚህ ባሻገር፣ ከጠ/ሚ/ሩ የቅዳሜ ጠዋት ቃለምልልስ የሚገኘው ቁም ነገር፤ ጋዳፊ ባለፈው ሰሞን ሰጥተውት ከነበረው ቃለምልልስ ጋር መመሳሰሉ ነው፡፡ ሕዝባቸው ሆ! ብሎ ለዴሞክራሲ ስለመነሳቱ የተጠየቁት ጋዳፊ፣ «የአልቃይዳ ሴራ ነው» ብለው ዓለምን ማስደመማቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡
የእኛው አቶ መለስ ደግሞ፣ «ሕዝባዊ ተቃውሞ የሚነሳ ከሆነ፣ ከበስተጀርባቸው ሻዕቢያ አለበት» ብለው ከወዲሁ ነግረውናል፡፡ እንደ ጋዳፊ እስከሚፈነዳ አልጠበቁም፤ ፈጣኑ መሪያችን!! «አዲስ አበባን በፈንጂ አናውጦ እንደ ባግዳድ ማድረግ የተሳነው ሻዕቢያ፣ በመንገድ ላይ ነውጥ ባግዳድ ሊያደርጋት ምሏል» ብለው አርድተውናል፡፡
በሌላ አነጋገር፣ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲው ጥያቄ ምንጭ ሕዝቡ ሳይሆን ሻዕቢያ ነው ማለታቸው ነው፡፡ ሕዝቡማ «በምርጫ ካርዱ ኢሕአዴግን ከስልጣን ሊያባርረው እንደሚችል ያውቃል» ብለውናል እኮ ጠ/ሚ/ሩ፤ ቀደም ብለው፡፡ እንደ ቱኒዚያ፣ ግብፅ እና ሊቢያ ጎዳና ላይ የሚወጣ ካለ፣ ወይ የሻዕቢያ ሴራ አስፈፃሚ ወይ ሰለባ ከመሆን አያልፍም፤ ለሃያ ዓመታት «ደግመን ደጋግመን በምርጫ ካርዳችን ኮንትራት እንደሰጠናቸው ጠ/ሚ/ራችን» ገለፃ ከሆነ፡፡
ጋዳፊ የቀበጣጠሩት የሞትና የሽረት ትንቅንቅ ላይ ሆነው ነበር፡፡ ድንግርግራቸው በቂ ምክንያት ነበረው፡፡ ለመከላከል እንኳን ፋታ ባጡበት ቅፅበት ነው ከአልቃይዳ ጀርባ ለመደበቅ የተተራመሱት፡፡ በአባባላቸው ዓለም አልተገረመም፤ ሳቀባቸው እንጂ፡፡
መለስ በአካል ምንም አይድረስባቸው እንጂ፣ በመንፈስ ከጋዳፊ የተሻለ ቦታ ላይ አይደሉም፡፡ ተጨንቀዋል፣ ተጠበዋል፡፡ የአእምሮ እረፍት የሚባል ነገር ከራቃቸው ውለው አድረዋል፡፡ «ዛሬ ነገ የጎዳና ላይ ተቃውሞ ቢነሳ ብለን እንቅልፍ ሳይወስደን አናድርም» ብለው ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት የፎከሩት መለስ ዜናዊ፣ የሻዕቢያን ስም ያለቦታው ሲያነሱ የተጨነቀው ገፅታቸው ፍንትው ብሎ ለመታየት በቅቷል፡፡
ሻዕቢያን ሙጥኝ ያስባላቸው ጭንቅ ነው፡፡ አይገርምም፤ ያስቃል እንጂ፡፡
ለመለስም ሆነ ለጋዳፊ፣ ከጭንቅ መገላገያው ዘይቤ በጣም ቀላል ነው፡፡ ድፍረትን፣ ቅንነትንና ጀግንነትን ግን ይጠይቃል፡፡
ስልጣንን በፈቃደኝነት መልቀቅ!!!
አሁኑኑ!!!
ምን እየጠበቁ ነው?
ፀሃፊውን ለማግኘት serk27@gmail.com
SOURCE ABUGIDA

Monday, December 2, 2013

የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ



ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በሰላማዊ መንገድ በሚደረግ ትግልና በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ዉይይቶች ቢመጣ የግንቦት 7 ምርጫ መሆኑን ንቅናቄያችን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። ግንቦት 7ን ሁለገብ ትግል ውስጥ እንዲገባ ያስገደደው የወያኔ እምቢተኝነትና እብሪት ብቻ ነው።
የግንቦት 7 ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሰሞኑ የወያኔ የእንደራደር መልዕክት እንደደረሰው በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ባጠቃላይ እንጂ ግንቦት 7ን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ ከድምዳሜ ላይ ደርሷል። ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ከሚያደርገው ትግልና እየከፈለ ካለው መስዕዋትነት ጋር በቀጥታ ግንኙነት አለው። በመሆኑም፤ ለቀረበልን ጥያቄ ግልጽ መልስና፤ ድርድር ስለሚባለው ጉዳይም ያለንን አቋም ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የኢትዮጵያ ሕዝብና የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለማቅረብ የሚያስችል ተጨማሪ አጋጣሚ አድርገን ወስደነዋል። በዚህም መሠረት ለቀረበልን ጥያቄ የሰጠነዉን መልስና አቋማችንን በድርጅታችን ድረ ገጽ ላይና በሌሎች መገናኛ ብዙሀን በኩል በይፋ ለመግለጽ ወስነናል።
በድርድር ስለሚመጣ ለውጥ ያለን የመርህ አመለካከት:
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እንዳደረግነው ድርጅታችን ከምሥረታው ጀምሮ የትግል ስልቱን ሲወስን እምነቱ አድርጎ የተነሳው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በሀገራችን በሰላማዊ መንገድና በድርድር ቢመጣ በእጅጉ የሚፈልገውና የሚመኘው መሆኑን ነው:: ድርጅታችንን ወደ ሁለንተናዊ ትግል የገፋው በመግቢያው ላይ እንደገለጽነው የወያኔ እብሪት ብቻ ነው:: የቀረበልን ምርጫ በባርነትና በውርደት መኖር ወይም ለነፃነት እየታገልን መሞት ቢሆን ኖሮ ንቅናቄያችን የሚመረጠው ምን ግዜም ለነፃነትና ለአገር አንድነት ታግሎ በክብር መሞት መሆኑን በተደጋጋሚ ለሕዝብ ግልጽ አድርገናል። ይህ የማይናወጥ አቋማችን ደግሞ ለይምሰል የተቀመጠ አቋም ሳይሆን ከልባችን የምናምንበትና ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አባላቶቻችንን ያሰባሰብንበት አቋም ነው። ዛሬ በትግሉ ግንባር የምንንቀሳቀሰውና ወደ ግባችን የሚወስደንን ተጨባጭ እርምጃዎች እየወሰድን ያለነውም በዚሁ አቋማችን ዙሪያ ነዉ።
ይህ አቋማችንና እምነታችን በአንድ ላይ ጎን ለጎን የሚሄዱ ሁለት መርሆችን አጣምሮ የያዘ ነዉ። አንደኛው፣ ሂደትን በሚመለከት ሁሌም ለድርድር ክፍት መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፣ ይህ የድርድር ሂደት እንዲያው ለለበጣ የሚደረግ ሳይሆን ወደሚፈለገው ነጻነት በአነስተኛ መስዕዋትነት ሊያደርስ ይችል ከሆነ በሩን ላለመዝጋት እንጂ፣ በምንም አይነት ዋና ውጤቱን፤ ማለትም ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ማድረግን፤ የሚቀይር ወይንም ከዚያ ያነሰ ውጤትን ለመቀበል መፍቀድን ፈጽሞ የማያመለክት መሆኑን ነው::
በእኛ በኩል ድርድሩን አስፈላጊና ጠቃሚ የሚያደርጉት መነሻ የፖለቲካ እሳቤዎችም ከእነኝሁ ሁለት መንታ ገጽታዎች የሚመነጩ ናቸው:: በድርድር ለሚገኝ ፍትሀዊና እውነተኛ ውጤት ክፍት መሆናችንን ሁሌም እናሳያለን፤ ነገር ግን ይህን የምናደርገው የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባትን ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት መከፈል አለበት የሚለውን መሠረታዊ የአካሄድ መርህ በመመርኮዝ እንጂ መርሀችንን ለድርድር ለማቅረብ እንዳልሆነ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል::
ስለዚህም:
ሀ)    የድርድሩ ውጤት የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ያረጋገጠ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በአስቸኳይ እውን ማድረግ መሆን ይኖርበታል:: ይህ ዋናው ግብ ሆኖ ከዚህ በመለስ የሚኖሩ በሂደት የሚገኙ አነስተኛ ግቦች ሊኖሩ ይችላሉ (ለምሳሌ የፖለቲካ እስረኞች ማስፈታት…ወዘተ):: ሆኖም በምንም አይነት ለእነኝህ መለስተኛ ግቦች ተብሎ ዋናውን ግብ የሚያሳጣ ወይንም ጊዜውን ያላግባብ የሚያስረዝም ድርድር፣ ድርድር ነው ብሎ ድርጅታችን አይቀበልም። ስለዚህም ዋናው የድርጅታችን ዓላማና ግብ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ፣ በፍጹም ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም:: በሥልጣን ላይ ባለው ኃይል በኩል ወደዚህ ግብ ለመድረስ ቁርጠኝነቱ በሌለበት ሁኔታ በሚደረግ ማንኛውም አይነት ድርድር ውስጥ ግንቦት 7 አይሳተፍም::
ለ)  በግንቦት 7 እምነት ማንኛውም ድርድር ወያኔ ከግንቦት 7 ጋር በተናጠል የሚያደረገው ሳይሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች ያካተተ መሆን ይኖርበታል:: ድርጅቶችን በተናጠል እየለያዩ “እንደራደር” ማለት በራሱ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ስሌትን የያዘ እሳቤ እንጂ፣ በዘላቂነት አገሪቱን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አገር ለማድረግ መፈለግን አያመለክትም:: ለአንድ ድርጅት ለብቻው የሚመጣ ወይም የሚጠቅም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የለም:: ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመፍጠር ፍላጎት ያለው ድርድር በአገሪቱ ያሉትን የተለያዩ የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ኃይሎችን ያካተተና ያመኑበት መሆን ይኖርበታል:: የሚደረገው ድርድርም ማን በስልጣን ላይ ይውጣ ወይንም የፖለቲካ ስልጣንን ባሉት ኃይሎች መሀከል እንዴት እናከፋፍለው የሚል የስልጣን ቅርምት ድርድር ሳይሆን፤ ሕጋዊና የሕዝቡን የሥልጣን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ ሁኔታ የፖለቲካ ስልጣን እንዴት እንደሚያዝ ፍትሀዊ የሆነ ሂደትን ለማስጀመር የሚደረግ ድርድር መሆን አለበት::
ሐ) ቀደም ብለን እንደጠቀስነው ይህ ጉዳይ የሚመለከተው አንድን ድርጅት ወይንም የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ነው:: ይህ እስከሆነ ድረስ እንዲህ አይነት ድርድር ከሕዝቡ በተደበቀ ሁኔታ በሚስጥር የሚካሄድበት ምንም ምክንያት የለም::
2)   ከዚህ በፊት ከወያኔ ጋር ከተደረጉ ድርድሮች ያገኘናቸው ተመክሮዎችና ከዚህ በመነሳት ወደፊት በሚደረጉ ምንም አይነት ድርድሮች እንዳይደገሙ ለመጠበቂያ የሚሆኑ ከአሁኑ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች
ከማንኛውም ወገን ጋር የሚደረግ ድርድር የተደራዳሪዎቹ ምንነት፤ ውስጣዊ ባህርያቸውን፤ ከተለምዶ ተግባራቸው ያላቸውን ተአማኒነትና ወደዚህኛው ድርድር ያመጣቸውን ምክንያቶች በበቂ ከመገንዘብ ጋር ተያይዞ የሚታይ ጉዳይ ነው:: ቃሉን አክባሪና ተዓማኒ ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ድርድርና ያለፈው ታሪኩ ምንም አይነት የተዓማኒነት ባህርይ ከማያሳይ ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድርም ሆነ ለድርድሩ የሚደረግ ዝግጅት ለየቅል ናቸው:: ይህ ማለት ግን ተዓማኒነት ካለው ኃይል ጋር ብቻ ነው ድርድር የሚካሄደው ማለት አይደለም:: በፍጹም ተዓማኒ ካልሆነ ኃይል ጋር የሚደረግ ማንኛውም ድርድር ግን ድርድሩ በእርግጥም ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መሆኑን የሚያሳዩ ጠንካራ መጠበቂያዎች (System of Verification) እንዲሁም ግልጽ የመተግበሪያ ሥርዓቶች (Implementation Mechanism) ሲደረጉለት ብቻ ነው ከምር ሊወሰድ የሚችለው:: ከዚህም ባሻገር ግን መጀመሪያውኑ ወደ ድርድር የሚመጣው ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሳይሆን በእዉነተኛ መንፈስ ከድርድር የሚመጣውን ውጤት በመፈለግ መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” ምልክቶች ሲያሳይ ነው በእርግጥም ወደ ድርድር የመጣው ከልቡ ድርድሩንና ከድርድሩ የሚመጣዉን ዉጤት ፈልጎ መሆኑን ለማመን የሚያስችለው::
ወያኔ ከተቀናቃኝ ወገኖች ጋር “ድርድር” ሲያደርግ የመጀመሪያ ጊዜዉ አይደለም:: እኛ እስከምናውቀው ድረስ ምናልባት በኃይል ይበልጡኛል ብሎ ከሚያምናቸው ወገኖች ጋር ካልሆነ በስተቀር፣ በረሃ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በማንኛውም ጊዜ ለቃሉ ታማኝ፤ ለመርሁ እውነተኛ፤ ለደረሰበት ስምምነት ተገዢ ሆኖ አያውቅም:: ይልቁንም ሶስተኛ አደራዳሪ ወገኖችን በሚያሸማቅቅና በሚያሳፍር መልኩ ውሸትን እንደ አዋቂነት፤ ማጭበርበርን እንደ ብልጠት፤ የተስማማበትን በገሀድ ማፍረስን እንደ የአመራር ብልሀት አድርጎ የሚያይ፤ ምንም እፍረትና ጨዋነት የሚባል ነገር ያልፈጠረበት እኩይ ኃይል ነው:: ከራሱ የድርጅት ጥቅምና በስልጣን ከሚገኝ የዝርፊያ ሀብት ማካበት ባሻገር፤ ለአገር ዘላቂ ጥቅም ብሎ የራሱን ጥቅም አሳልፎ የሚወስደው ምንም እርምጃ እንደሌለ በተግባር በተደጋጋሚ ያረጋገጠልን ኃይል ነው:: በግንቦት 7 ውስጥ ያለን ወገኖች ይህንን የወያኔ ባህርይ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ሌሎች ጽፈውት ያነበብነው ሳይሆን፣ እራሳችን በተግባር በተሳትፈንበት ሂደት ያገኘነው ጥልቅ ግንዛቤ ነው:: ይህንን ደግሞ በአንድ አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ከድርጅቱ ታሪክ ጋር የተጣበቀ፤ በአመራር አባላቱ ላይ እንደ ግል ባህርይ የሰረጸ መሆኑን እስክንገነዘብ ድረስ በተደጋጋሚ የተመለከትነው ነው:: ስለዚህም ከዚህ ኃይል በኩል የሚመጣን የ “እንደራደር” ጥያቄ ከዚህ በፊት እንዳደረገው ለገባበት የፖለቲካ ውጥረት ማስተንፈሻ፣ ለውሸት ፕሮፓጋንዳው መጠቀሚያ፤ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ መሰብሰቢያ፤ የዴሞክራሲ ታጋዮችን ትጥቅ ማስፈቺያና ወኔ መስለቢያ አድርጎ እንዲጠቀምበት በፍጹም አንፈቅድለትም:: ስለዚህም ከላይ በመርህ ደረጃ ከጠቀስናቸው ሶስት ጉዳዮች በተጨማሪ ምንም ዓይነት ድርድር ከመደረጉ በፊት ወያኔ ጉዳዩን ከምር የወሰደው መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” እርምጃዎች መውሰድ አለበት ብለን እናምናለን::
እነኝህም፣
ሀ)  ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት:: ይህ ደግሞ በግልጽ     የሚታወቁ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን በድብቅ የተቋቋሙ ማጎሪያና ማሰቃያ ቤቶች ያሉትን ሁሉ ማጠቃለል አለበት።
ለ)  በሕዝብ በተለይ በተቃዎሚ ኃይሎች ላይ ወያኔ በየቀኑ እያካሄደ ያለውን ወከባና እንግልት ባስቸኳይ ማቆም፣ ሰብዓዊና የዜግነት መብታቸውን ማክበር አለበት።
ሐ)   በፖለቲካ ምክንያት ከዚህ በፊት የተወሰዱ ሁሉም ዓይነት ፍርድ ተብዮ ውሳኔዎች እንዲሻሩ ማድረግ፤ በሂደት ላይ ያሉ ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ምንም አይነት ክሶችን ማቋረጥ አለበት።
መ)   ሕዝብን በፍርሃትና በስጋት ለማቆየት ሆነ ተብለው የወጡ አፋኝ ህጎችን በአስቸኳይ ማንሳት አለበት።
ሠ)   ማንኛውም ድርድር ገለልተኛ የሆኑ ሶስተኛ ወገኖች ባሉበት፤ የድርድሩ ሂደት በምስልና በድምጽ ተቀርጾ በገለልተኛ ወገኖች እጅ ብቻ የሚቀመጥ፣ የድርድሩ ቦታም የተደራዳሪ ወገኖች በጋራ በሚስማሙበት ቦታ መሆኑን መቀበልና ይህንንም በግልጽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቅ አለበት።
እነኝህ ከላይ ያስቀመጥናቸው በወያኔ በኩል የሚወሰዱ “የመተማመኛ” እርምጃዎች ለተቃዋሚዎች ተብሎ የሚወሰዱ እርምጃዎች አይደሉም:: ወያኔ እነዚህን እርምጃዎች ለመውሰድ ቁርጠኝነት ሳይኖረው ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት የሚደረግ ድርድር ላይ ከምር ይሳተፋል ብለን ማመን በፍጹም ስለማንችል ነው ::
እስከዚያው ድረስ ግን ግንቦት 7ም ሆነ ሌሎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት በቁርጠኝነት የምንታገል ኃይሎች፣ ወያኔ እነኝህን የመተማመኛ እርምጃዎች እስኪወስድና ቀደም ብለው በተቀመጡት መርሆች መሠረት በሚደረግ ድርድር በተግባር ሊመነዘር የሚችል ስምምነት፣ አልፎም ለምንም አይነት ማጭበርበርና መንሸራተት እድል የማይሰጥ ጠንካራ መጠበቂያዎች መኖራቸው እስኪረጋገጥ ድረስ፣ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን የምንገፋበት እንጂ በምንም አይነት ለአንድ አፍታም ቢሆን በድርድር ስም የማንዘናጋ መሆኑን አበክረን እናስታውቃለን::
የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣
ኅዳር 23፣ 2006 ዓ:ም