Saturday, November 30, 2013

ቴዎድሮስ አፍሮ ክስ ይቀርብበታል ተባለ ፣ፕሮሞተሮቹም ችግሩን ለመፍታት እየጣርን ነው ብለዋል ።

በሰሜን አሜሪካ ከፍተኛውን የቴዲ አፍሮ ፕሮሞሽንንን በመስራት የሚታወቀው( KMF INC ) ጋር የረጅም ጊዜ ስራ እንዳላቸው እና የተደነቀለት ስራዎችን መስራታቸው ይታወሳል ።ሆኖም እንደ ዉላቸው መሰረት መሄድ ያልቻሉት በቴዲ አፍሮ ውል ማፍረስ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል ። http://www.maledatimes.com/?p=9888




Friday, November 29, 2013

"The Ethiopian Gov. Is Part Of The Problem" -Abebe Gellaw

SaharaTV’s Adeola Interviews Abebe Gellaw on deportation of Ethiopians in Saudi Arabia




በሳውዲ አገር የተፈጸመው የኢትዮጵያውያን ውርዴት ያተስተናገደው ማን እንደሆን የማያውቅ ወይም የሚጠራጠር ካለ መልሱ (ተ.ሀ.ሕ.ት.) ነው። | Zehabesha Amharic

በመጀመርያ የወገናችሁ ሥቃይና መከራ አንገብግቧችሁ ሲያለቅሱ አልቅሳችሁ፣ሲከፉ አብሮ ለምከፋት፣ሲቸገሩ ችግራቸውን አብሮ ለመጋራትና በደላቸው የናንተ በደል መሆኑን ለማሳዬት በዓለም ዙርያ ለምትገኙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በሙሉ በጣም ኮርቸባችሁ አለሁ። read more
በሳውዲ አገር የተፈጸመው የኢትዮጵያውያን ውርዴት ያተስተናገደው ማን እንደሆን የማያውቅ ወይም የሚጠራጠር ካለ መልሱ (ተ.ሀ.ሕ.ት.) ነው። | Zehabesha Amharic

MUST WATCH!!!Very heart touching speech and poem by beloved Ethiopian atrist Ayalew Mesfin.

A great speech by beloved Ethiopian artist Ayalew Mesfin, Thank you Ayalew for raising your voice and solidarity on Ethiopians in Saudi. You have big place on Ethiopians heart. click the link below

Another a Heart touching News from Beirut, Lebanon (ከቤሩት የተሰማ አሰቃቂ መረጃ)

ከቤሩት የተሰማ አሰቃቂ መረጃ (ይህን ቪድዮ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ እንዲያዩት አይመከርም)
ወደ ዘ-ሐበሻ ዝግጅት ክፍል በፌስቡክ የግል መልዕክት አንድ እህት ብታነጋግሩኝ አሳዛኝና ማንም ያልዘገበው መረጃ ቤሩት ውስጥ የተፈጸመ አቀብላችኋለሁ አለችን። ፈቃዳችንን ገልጸን ስልኳን ተቀብለን ወደ ቤሩት ደወልንላት። አነጋግርናት። ሌሎችንም እንዲሁ አንጋገርን። ከዚያም የሚከተለው አሳዛኝ መረጃ እንዲህ ተቀናበረ።


Thursday, November 28, 2013

Breaking News: Four People Struck and killed by Car Accident in Addis Ababa | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Breaking News: Four People Struck and killed by Car Accident in Addis Ababa | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

«ሰው ለሰው» የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ።

«ሰው ለሰው» የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ።

 ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ ይገዛሉ ፤ ፍትህን ይረግጣሉ ፤ በሰው ህይዎት ይነግዳሉ፡ ፤ ሰው ያስገድላሉ፤ ህዝብን ያስለቅሳሉ፤ በወንጀል ይነግዳሉ፤ ሰው በላ እና ነፍሰ ገዳይ አምባገነን ናቸው ሲሉ እንደሚተቹዋቸው ይታወቃል።
ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ድራማው የመንግሰትን ስራ እያንቋሸሸ ፤ ከመንግስት ፍላጎት ውጭ እየሄደ በመሆኑ እንዲቀየር የኢቲቪን አስተዳዳሪዎች ማዘዛቸውን የወስጥ ምንጮች ገልጸዋል። ውስጥ አዋቂዎች ድራማው የወ/ሮ አዜብ መስፍንን ታሪክ የተከተለ እና አብዛኛውን የመንግስት ባለስልጣናት የመክበሪያ ዘዴ የጠቆመ በመሆኑ መንግሰት እንደ ነገሪ ሰሪ ተመልከቶታል ብለዋል። ጉዳዩ ዙሪያ የኢቲቪን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

Wednesday, November 27, 2013

ፍትሕና ነፃነት እንፈልጋለን

(በ ለምለም ሀይሌ) 
ባሁኑ ግዜ በሀገራችን ያለውን ሰላማዊ ትግል አስመልክቶ የተለያዩ ነጥቦችን ማንሳት ይቻላል። ከአመት በላይ ያስቆጠረውን የድምጻችን ይሰማ ሰላማዊ ትግል፣ የሰማያዊ ፓርቲ እና የአንድነት ፓርቲ እያደረጉት ያለውን ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ይህ ነው የሚባል አይደለም። በተለይ በ 2009 ዓ ም በወጣው ANTI TERRORISM LAW በታጠረውና ምንም አይነት የመናገር ነጻነት በሌለበት ሀገር ውስጥ ሆነው ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው በሀገራችን ያለውን የመብት ረገጣ፣የዜጎች ያለአግባብ መፈናቀል ይብቃ በማለት እያደረጉት ያለውን ከፍተኛ ትግል ይህ ነው የሚባል አይደለም። ይህ ነገር ለሌሎች አስተማሪና በተለይ እዚህ ነጻነት ባለበት ሀገር ለምንኖር ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የበለጠ እንድንሰራና እንድንታገል የሚያደርግ ነው።
የሰማያዊ ፓርቲ በቅርብ ግዜ እያደረገ ያለው ከፍተኛ ትግልና ሰላማዊ ሰልፍ የሚኖረውን የህዝብ ብዛት ስንመለከት፣ ለወጣለት አላማ ምን ያህል ቆርጦ የተነሳ ህዝብ እንዳለ እንረዳለን። ሆኖም ግን በዚህ ትግል ውስጥ የሚደርስባቸው እና እየደረሰባቸው ያለ ከፍተኛ የሆነ ችግር እንዳለ ግልጽ ነው።
በተለያዩ ቦታዎች የቅስቀሳ ስራቸውን እንዳያደርጉ ከመታገድ ጀምሮ እስከ ድብደባና እስር ያሉ ጉዳቶች ይደርስባቸዋል። ያልተፈቀደላችሁ ቦታ ቅስቀሳ አካሂዳችዃል፣ እንዲሁም ያልተፈቀደላችሁ ቦታ ሰላማዊ ሰልፍ ወታችዃል በሚሉ ጥቃቅንና ተልካሻ ምክንያቶች ከሚድያ ሽፋን ውጭ በመሆን በአባላቱ ላይ እየደረሰ ያለውን ድብደባና እስር፣ ይህን ሰላማዊ ትግል ለማስቆም ከተደረጉ ጥረቶች መሀከል ይጠቀሳሉ።
ነገር ግን የትግሉ መሪዎች ይህን ሁሉ በገዢው መንግስት እየደረሰባቸው ያለውን ችግር በመቋቋም የያዙትን አላማ ከግብ ለማድረስ ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ለ22 አመት በአንድ ጨቋኝ መንግስት ስትመራ ለቆየች ሀገር ትክክለኛና ደሞክራሲያዊ የሆነ አስተዳደር ለማምጣት ከፍተኛ የሆነ መስዋእትነትን ይጠይቃል።


ስለዚህም ይህንን በአለም ያለ የነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን እና በተለይም በሀገር ውስጥ ላለው ከማንም ቀድሞ ጥቃት ለሚደርስበት ወገናችን ከጎን በመሆን ይህን ሰላማዊ ትግል ከዳር ለማድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል በጋራ በመሆን በወያኔ መንጋጋ ውስት ወድቃ ያለችውን ሀገራችንን ነጻ እናውጣት።

Sunday, November 24, 2013

“እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ..” ራውዳ ጀማል – ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያዊት (ቃለ ምልልስ)

“እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ..” ራውዳ ጀማል – ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያዊት (ቃለ ምልልስ)

Rawda Jemal
በሃገር ቤት እየታተመ የሚወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ቃለ ምልልሱ ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም ትዘግባቸው የነበሩ የሳዑዲ ሕይወቶችን የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ያደረገችውን ቃለምልልስ ለአንባቢዎቻችን እንደወረደ ይኸው፦
ራውዳ ጀማል ትባላለች፡፡ የሃያ ዓመት ወጣት ናት፡፡ ስለራስዋም ሆነ በሳኡዲ ስላሉ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ ስታወራ እያለቀሰችና እየተወራጨች ነው፡፡ ለማነጋገር ስቀርባት “ወንድ ከሆናችሁ ጋዜጠኞች ነን፣ የህዝብ አፍ ነን ካላችሁ፤ እዚህ ተቀምጣችሁ፣ “ሁለት ሰው ሞተ” እያላችሁ ከምታቅራሩ ሳኡዲ ሂዱና በየቀኑ ሁለት ሶስት ሰው የሚሞትበትን እልቂት ተመልከቱ፣ “ሰዎቹን ምን እየሰራችሁ ነው?” ብላችሁም ጠይቁልን” አለችኝ። መቅረፀ ድምፄን ሶስት አራት ጊዜ ያስጠፋችኝ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ለቃለ ምልልስ ፈቃደኛ ሆነችልኝ፡፡
ስንት ዓመት ቆይተሽ መምጣትሽ ነው?
ከሁለት ዓመት በኋላ ነው የመጣሁት፡፡ እስከ አስረኛ ክፍል የተማርኩት አዲስ አበባ ቢሆንም፤ የኮምቦልቻ ልጅ ነኝ፡፡
እንዴት ነበር የሄድሽው?
በፓስፖርት… በኮንትራት ነበር የሄድኩት … ካላስ! የሰውየው ልጆች ግን “የማይሆን” ፊልም ተመልከቺ እያሉ ያስቸግሩኝ ነበር፡፡ ሲመረኝ ጠፍቼ ወጣሁ፡፡ ከዚያም ከጓደኞቼ ጋር በነፃነት ቤት ተከራይተን እየኖርን፣ በ1800 ሪያል ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩኝ፡፡ ቤተሰቤንም ገንዘብ እየላኩ እረዳ ነበር፡፡
ወደ አገርሽ እንዴት ተመለስሽ?
ውጡ ሲባል… ረብሻ ሲነሳ.. ጓደኞቻችን ሲሞቱ.. ሲደፈሩብን.. ‘ድሮም ስደተኛ ክብር የለውም’ ብዬ ተመልሼ መጣሁ..ከሚገሉኝ ከሚያበለሻሹኝ ብዬ እጄን ሰጠሁ፡፡ ብዙ ኢትዮጵውያኖች ችግር ላይ ናቸው.. እባካችሁ ድረሱላቸው፡፡ ብርዱም ፀሃዩም ሲፈራረቅባቸው.. ያሳዝናሉ፡፡ ብዙ ያልመጡ አሉ፤ መምጣት እየፈለጉ፡፡ ስቃይ ላይ ናቸው፡፡ እኔ አሁን አስራ ሶስት ቀን ታስሬ ነው የመጣሁት፡፡ እስቲ ስለ እስሩ ንገሪኝ … ሁለት ቀን ያለ ምግብ ያለ ውሃ ነው የታሰርነው። ከዛ በኋላ ግን ጥሩ ምግብ ሰጥተውናል፣ ጥሩ መኝታም አግኝተናል፡፡ ብዙዎቹ ግን ከእኛ የባሰ ችግር ላይ ናቸው፡፡ መጠለያ ያላገኙ አሉ… ኤምባሲያችንም አይሰማም እንጂ ስንት ጊዜ ደውለን ተናግረናል መሰለሽ፡፡ ግን የሚሰማ የለም፡፡ ከአገራችን ውጡ ካሉ በኋላ ትዕግስት ያጡና መልሰው ይዩዙናል፡፡ በዛን ጊዜ አበሻው፣ ሻንዛ/ጩቤ ይመዛል፡፡ ፖሊስ ራሱን ለማዳን ይተኩሳል። እኔ እንደውም ደህና ነኝ፤ እዛ ላሉት ድረሱላቸው። በምድረ ዱርዬ እየተደፈሩ ነው ያሉት /ለቅሶ/ ስንት ህፃናት አሉ የሚሞቱ፣ የሚታመሙ፡፡ ስንመጣ ደሞ፤ ሻንጣ አትያዙ ተብለን ተመናጭቀን…በጥፊ ተመትተን..መከራችንን በልተናል፡፡
ወንዶችና ሴቶች ለብቻ ነበር የተቀመጣችሁት?
የተቀመጣችሁት አትበይ! የታሰራችሁት በይ፡፡ … የሴት እስር ቤት ለብቻው ነው በሴቶችና በህፃናት ለቅሶ የተሞላ ነው፡፡ እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ…/ለቅሶ/
አሁን ቤተሰብ እየጠበቅሽ ነው?
ነበረ ግን ሻንጣዬ ጠፋብኝ፡፡ በርግጥ ጤነኛ ሆኖ መምጣትም ቀላል አይደለም፡፡ እዛ ያሉትን ጥለናቸው ስንመጣ እያለቀስን ነው፡፡ እስር ቤቱ ውስጥ አንድ እርጉዝ ሞታብናለች፡፡ እዛው እስር ቤት እያለን ምጥዋ መጣ፤ ግን የህክምና እርዳታ ባለማግኘትዋ ሞተች፡፡
እስር ቤት ያሉት ምን ያህል ይሆናሉ?
ሰማኒያ ክፍል አለ..በየክፍሉ ስልሳ አምስት ስልሳ አምስት ሰው ነው ያለው፡፡ መካሲመሺ እስር ቤት ይባላል፡፡ የወንድና የሴት እስር ቤት የተራራቀ ነው፡፡ በጣም ረጅም ከመሆኑ የተነሳ በመኪና እንጂ በእግር አይሞከርም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በከተማው ያለው እስር ቤት ሞልቶ የመዝናኛና የስብሰባ አዳራሹን ሁሉ እስር
ቤት አድርገውታል፡፡ የተደፈሩት የሞቱት..ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡ አንዷን እርጉዝ ለሶስት ሲደፍሯት ሞታለች፡፡
የሌሎች አገር ስደተኞችም እየወጡ ነው ተብሏል…
አዎ፡፡ ኢትዮጵያዊው ከበደሉ ብዛት የተነሳ እየተናነቀው እኮ ነው ግጭቱ የሚከረው፡፡
ሚስቱን እህቱን ከእጁ መንትፈው ሊወስዱበት ሲሉ ነው ጦርነት የሚነሳው፡፡ አበሻ ወንድ እየሞተ ያለው ‹‹ሴቶቻችንን አትንኩብን..›› ስለሚል እኮ ነው፡፡ ኤምባሲው ሊደርስላቸው ይገባል፡፡