Tuesday, October 15, 2013

Nhatty Man & Jacky Gosse - Fim Esat [NEW! Music Video Clip] - ይህ ትውልድ ፍም...

በጣም ተወዳጅ የሆነው የ ናቲና የ ጃኪ ፍም እሳት የሚለውሙዚቃ በስተመጨረሻ ክሊፑ ተለቋል። በኔ አመለካከት የሙዚቃው መልእክት በኢትዮጵያ የእግር ክኳስ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገውና  ባሁኑ ወቅት በጣም ከፍተኛ ለውጥን ላመጣው ዋልያችን ብቻ ሳይሆን፣ የወያኔ የእግር እሳት በመሆን ጨቛኙን የኢትዮጵያ መንግስት በማንኛውም አቅጣጫ እያፋጠጠ ላለውና እምቢ መረገጥ፣መታፈን፣መጨቆን በቃኝ ላለው የዚህ ዘመን ትውልድ ነው ባይ ነኝ። እስቲ እናንተም ክሊፑን አይታችሁ የራሳቹን አስተያየት ስጡበት። እነሆ ክሊፑ!

ለምለም ከኖርዌይ




Sunday, October 13, 2013

ስብሃት ነጋ ወንጀል ፈፀሙ፤ በአሁን ሰአት በፖሊስ እየታደኑ ነው – ከኢየሩሳሌም አረአያ


ከኢየሩሳሌም አረአያ
sebehatበአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ከአንድ ሰአት በፊት ስብሃት ነጋና አብሯቸው የነበረ ግለሰብ በአንድ ኢትዮጲያዊ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመው ማምለጣቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። መስፍን የተባለው ኢትዮጲያዊ በአሁኑ ሰአት በሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን የሲቪሊቲ ሩም ፓልቶክ አዘጋጅ አባ መላ በስልክ አግኝቶት ስለሁኔታው ያነጋገረው ሲሆን፤ መስፍን እንደገለፀው በድብደባው ጅርባው እንደተጎዳና ብዙ ደም እንደፈሰሰው ገፆዋል። እነስብሃት ድብደባውን ሲፈፅሙ በቅርብ ርቀት ቪዲዮ እየተቀረፁ እንደነበረና ይህኑን ማስረጃ ለፖሊስ መስጠታቸው ታውቋል። ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ፖሊስ በአካባቢው ፈጥኖ የደረሰ ሲሆን፣ በአሁን ሰአት እነስብሃትን ለመያዝ ፖሊስ መሰማራቱ ታውቋል።