Saturday, February 22, 2014

Ethiopia: Abebe Gellaw Hailemedhin Abera

“በአለም ዙሪያ የሚኖር ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወጣቱን ኢትዮጵያዊ ጀግና ሃይለመድህን አበራን በአደባባይ
መደገፍ ይገባዋል። ወያኔ በቤተሰቡ ላይ ጫና እያደርገ የሚሰራውን የከሰረ ፕሮፓጋንዳ አጥብቀን እናወግዛለን።”Abebe Gellaw

Monday, February 17, 2014

የኢትዮጵያ አውሮፕላን በገዛ ረዳቱ ጠለፋ ተደረገበት… ለምን… ?

የኢትዮጵያ አውሮፕላን በገዛ ረዳቱ ጠለፋ ተደረገበት… ለምን…  ? (ከአቤ ቶክቻው)
ዛሬ ወደ ሮም ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን መጠለፉን ሰማን። ማነው እንዲህ የደፈረን ብለን አቶ ሬደዋንን ብንሰማቸው ጊዜ “አውሮፕላኑ ሱዳን ላይ አርፎ ነበር ምናልባት ጠላፊዎቹ ያኔ ይሆናል የገቡት” ብለው ተናገሩ።  ኋላ ላይ ሲጣራ ግን ጠላፊው የአውሮፕላን አብራሪው ረዳት  መሆኑ ተሰማ፤  ረዳቱ ጠለፋውን የፈፀመው ዋናው አብራሪ በአውሮፕላኑ መፀዳጄ ቤት ጎራ ባለበት ሰዓት ነው።
ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ…
መላ ምት አንድ፤
ዋና አውሮፕላን አብራሪው ፓይለት በሰላም እየበረረ ሳለ መንገድ ላይ የመፀዳዳት አምሮቱ መጣበት እና ረዳቱን፤ “በሰማይ የሰጠውህን በሰማይ እቀበልሃለሁ” በሚል፤ አደራ በሎት መፀዳጃ ቤት ወገቡን ሊፈትሽ ገባ። ይሄን ጊዜ ረዳቱ ሆዬ “ይሄ ሰውዬ ከመፀዳጃ ቤቱ ሲመለስ ሮም አድርሶ ከዛምም ወደ ፍትህ አልባዋ ሀገሬ ከሚመልሰኝ አሁን መሪውን እንደጨበጠኩ የራሴን እድል በራሴ ለምን አልወስንም” አለ እና … መሪውን አለቅም አለ። ሰዊስ ጄኔቭ ላይም ጥገኝነት ትሰጡኝ እንደሆን ስጡኝ ብሎ አሳረፈው።
መላ ምት ሁለት፤
ዋና አብራሪው እና ረዳቱ ቀድሞውኑ ተነጋግረው ነበረም ይሆናል። (ምንም እንኳ ይቺ ዋና አብራሪውን የምታስፎግር መላ ምት ብትሆንም ከጠረጠርን ጠረጠርን ነውና እንናገራለን)
ገና ከኢትዮጵያ ሰማይ ላይም ሳይወጡ፤ ረዳቱ እና ዋናው ኢትዮጵያ መሬት ላይ እያሉ ምሬቶቻችውን ሲያወጉ ነበር አሉ። በተለይ ረዳቱ የደረሰበትን አስተዳደራዊ በደል ሁሉ ዘረዝሮ ለዋናው አብራሪ በነገረው ጊዜ ዋና አብራሪውም በረዳቱ የደረሱ በደሎች በሙሉ በሱም እንደ ደረሱ ነግሮት ስቀሰቅ ብለው ተላቀሱ። ከዛም ረዳቱ አለው፤ “ላንተ እና ለሀገሬ እግዜር መላ እንዲያበጅላችሁ እፀልያለሁ ለእኔ ግን አንድ መላ አብጅቻለሁ” አለው። ቀጠለናም አንተ የምትተባበረኝ አንድ ነገር ብቻ ነው… ሲል ነገረው። “አንተ የሁነልህ እንጂ ችግር የለም ምን ለተባበርህ…” አለው ዋናው አብራሪ… በነገው በረራ የሆነው ቦታ ላይ መፀዳጃ ቤት ገብተህ ትንሽ ቆይታ አድርግ…! አለው አደረገም የሆነው ሁሉም ሆነ።
ከዚህ  ምን እንገነዘባለን፤
አንድ ወዳጃችን በፌስ ቡክ ገፁ “ነገ ከነገ ወዲያ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አውሮፕላን ጠለፈው ጥገኝነት ጠየቁ  የሚል ዜና መስማታችን አይቀርም” ብሎ እንደጠረጠረው በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የደላው ማንም እንደሌለ በቅጡ  እንረዳለን። ከአውሮፕላን ረዳት እስከ ታክሲ ረዳት እና ቤተሰብ ረዳት በሙሉ በፍትህ እጦት “የተማረረበት ሁኔታ ነው ያለው”
በመጨረሻም፤
ያማንማረርባት እና የማንባረርባት ኢትዮጰያ ትመጣ ዘንድ እንፀልያለን።