Thursday, December 19, 2013

(ድንቅ መጽሔት ዜና ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአደጋ ለጥቂት ተረፈ።


(አሁን የገባ ዜና) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንድ 767 መንገደኞችን እንደጫነ አሩሻ ታንዛኒያ በሚገኝ አንድ ትንሽ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ መገደዱ ታወቀ። አየር ማረፊያ ትንሽና ለቦይንግ 767 ዓይነት ትላልቅ አውሮፕላኖች የተሰራ ባለመሆኑ አውሮፕላናችን ያረፈው እንደምንም በማረፊያ ሜዳው ጫፍ ድረስ ሄዶ በመቆም ነው። ይጓዝ የነበረው ወደ ዛንዚባር ነበር የሚለው የወሬ ምንጩ .. ነገር ግን እዚያ ደግሞ ሌላ አውሮፕላን ተበላሽቶ በመቆም ማረፊያውን ስለዘጋው ወደዚህ ሊመጣ ችሏል ነው የተባለው። ቢሆንም ፣ ከዚህ ከጠባቡ አየር ማረፊያ ይልቅ ለምን ወደ ናይሮቢ ወይም ወደዳሬሰላም እንዳልተመራ ምርመራ መደረግ አለበት ተብሏል። አንዳንዶች ግን በውስጡ የያዘው ነዳጅ ሌላ ቦታ ለመውሰድ በቂ አልነበረም ነው የሚሉት። 

በ ኢቲ 815 የበረራ ቁጥር የተመዘገበው ይኸው አውሮፕላን ፣ አሁን በድንገትና ሳይታሰብ ካረፈበት ማረፊያ እንዴት ተነስቶ እንደሚሄድም ገና የሚያጠያይቅ ነው ይላል ዜናው - ምክንያቱም አውሮፕላኑ ትልቅ፣ የአየር ማረፊያው መንደርደሪያ ደግሞ ትንሽ በመሆኑ ለመነሳት አስቸጋሪ ይሆንበታል። በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማብራሪያ እስካሁን አልሰጠም።