ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም
ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ አዲሱ ዬኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን ስንሰማ የስራት ለውጥ ለናፈቀን ኢትዮጵያውያን ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም የሚለውን የሃገራችን ብሂል ሳናስታውስ ኣንቀርም።
እኛን የናፈቀን መች የፕሬዝዳንት መለዋወጥ ሆነና፣ነገር ግን የኢትዮጵያን ህዝብ የራበው ሰላምና ፍት ህ የሰፈነባት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድር አዲስ አሰራርና የስራት ለውጥ ነው እንጅ፣ ከውጭ አምባሳደሮች የሻይና ቡና አጣጭ እንዲሁም ከችግኝ ተከላ ያላለፈ ፕሬዝዳንትነት ለራሱ ካልሆነ በስተቀር ለሃገራችን ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም።
ለማንኛውም ለቀድሞው ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ እንኳን ከቤተመንግስት ወደ ሌላኛው ቤተመንግስቶት አሸጋገሮት፣እንዲሁም ሌዲሱ ፕረዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ደግሞ መልካም የችግኝ ተከላ እና የ ሪባን መቁረጫ ግዜ ይሁንሎት እላለሁ።
ለምለም ከ ኖርዌይ