ይህ ከሰሞኑ የወጣ ''ማነው ሚለየው ይህ ትውልድ ፍም እሳት ነው'' የተሰኘው የናትናኤል እና የጃኪየጋራ ሙዚቃ ባሳለፍነው ቅዳሜ ሴፕቴምበር 28, 2013 በኖረዎይ ኦስሎ የተደረገው የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ካየሁትና ካስተዋልኩት ነገር ጋር አንድ ሆነበኝና ዘፈኑን ደግሜ ደጋግሜ ባዳምጠውም አልወጣልሽ አለኝ።
ይኸውም በቦታው የነበርን ሰዎች እንዲሁም ዝግጅቱን በቀጥታ በ ፓልቶክ የተከታተልን ሰዎች እነደምናስታውሰው በአይነቱ ለየት ያለና እጅግ በጣም የደመቀ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እነደነበር ይታወሳል።በእለቱም ከነበሩት የክበር እንግዶች የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ማሩ በተጨማሪ ከተለያየ የኖርዎይ ክፍለ ሃገራት የመጡ ታዳሚዎች እና ከ ኖርዎይ ውጭ ከሌሎች የ አውሮፓ አገሮች የመጡ አገር ወዳዶችም ተገኝተዋል።
ፕሮግራሙን በይበልጥ ያማረና የደመቀ ካደረጉት ነገሮች አንዱም ለክብር እንግዶቹ የተደረገላቸው በወጣት ታጋዮች ወታደራዊ አለባበስና ስርአት የቀረበው ወታደራዊ አቀባበል ሲሆን እነዲሁም በየሰዉ እጅ ሲውለበለብና ሀገራዊ ስሜትን ሲቀሰቅን የነበረው የ ኢትዮጵያ ባንዲራ ነው።
በዚህም ቀን በተደረጉት የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች 48,633 የኖርዌጅያን ክሮነር የተገኘ ሲሆን ። ይህ ገቢ ከምግብ ሺያጭ ፣ ከመግቢያ ትኬት፣ ከቲሸርት ሺያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች ሺያጭ ሳይጭምር መሆኑ ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ሀገራዊና ፖለቲካዊ ውይይቶች ተደርገዋል።
በዝያም ቀን በሰው ሁሉ ፊት ላይ ያነበብኩት ነገር ቢኖር ከፍተኛ የሆነ ይሀገር ፍቅር ስሜት እንዲሁም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለማምጣት የሚሻ ልብ በነዚያ በፍም እሳትና በማይደፈሩ ትውልዶች አይን ላይ ሳይ የተሰማኝ ስሜት የዚህ ትውልድ አንዱ ኣካል በመሆኔ ከፍተኛ ኩራት ነው። እውነትም ፍም እሳት ለወያኔ የእግር እሳት።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
ለምለም ሀይሌ ከኖርዌይ