Thursday, November 7, 2013

የባቡር ቀለም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምኑ ነው ወገኖቼ?

አረ አሁንስ የ ኢትዮጵያ መንግስት ከጥርሴ አልፎ  አይኔን እያሳቀኝ  ነው ። የሚያስተዳድረውን መንግስት መምረጥ ያልቻለና ለ 22 አመት በአንድ መንግስት ቁጥጥር ስር ለዋለ ምስኪን ሕዝብ አሁን የባቡር ቀለም ምረጥ መባሉ ምን የሚሉት ነው? አረ ለመሆኑ የባቡር ቀለም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምኑ ነው ወገኖቼ? የለት ጉርሱን ማግኘት ተስኖት ፆሙን ለምያድረው ምስኪን ደሃ ሕዝብ የባቡር ቀለም ምኑ ነው? ስልጣን ላይ ከወጣበት ግዜ አንስቶ አሁን ያለንበት ግዜ ድረስ ሕዝቡን ምንም አማክሮ የማያውቅ መንግስት አንዲሁም ሁሉን በገዛ ፈቃዱ ሲፈልጥ ሲቆርጥ የነበረ መንግስት ሌላው ይቅርና የምታዩትንም ሕልም ከኔ ፈቃድ ዉጭ ያለአግባብ አንዳታዩ ማለት የቃጣው መንግስት አሁን ተነስቶ የባቡር ቀለም ማስመረጡ ምን የሚሉት ነው? ወይስ የህዝቡን ሃሳብ የሚሰማ መንግስት አንደሆነ በዚህ ለማሳየት ነው።

 እንደኔ አንድኔ ግን የህዝቡን ልብ ትርታ ማዳመጥ በዚህ ሳይሆን ዛሬ ወገን ደራሽ አጥተው የትም ለወደቁትና ልክ ወላጅ እንደሌለው ሕፃን ልጅ እየተንከራተቱ እንዲሁም የአረብ ፖሊስ መጫወቻ ለሆኑት ወገኖቻችን አለሁ ያገባኛል በማለት ለሕዝቡ ተቆርቃሪነቱን በማሳየት ይመስለኛል። ዉሃ ቢወቅጡት አምቦጭ ነውና ነገሩ አምባገነኑ የኢትፖጵያ መንግስት ህዝቡ የሚለውን ሰምቶ የሚቀይረው ነገር ባይኖርም አኔ የተሰማኝን ከማለት ወደዃላ አልልም።   
ቸር እንሰንብት 

ለምለም ከኖርዌይ 
      

No comments:

Post a Comment