Saturday, February 28, 2015

ሰበር ዜና: የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ!

ሂሩት መለሰ – ከሮተርዳም
ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 – በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል።

የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ – የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ሰው ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፎላ ይባላል። በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል ሆኖ ለረጅም አመታት አገልግሏል። ወያኔ ስልጣን ሲቆጣጠር ለፖለቲካ ተሃድሶ አዋሳ ደቡብ ጦር ቅጥር ግቢ ተላከ። በተሃድሶ በነበረበት ጊዜ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የሰራዊቱ አባላትን ለወያኔ በማጋለጥ ታማኝነቱን ሲያሳይ እንደነበር የዚህ ዜና ዘጋቢ እማኝ ነው። የበርካታ ኢትዮጵያውያን ደም በእጁ ያለው አለማየሁ ከተሃድሶው ከወጣ በኋላ እስራኤል ገደቡ (የፓልቶክ ስሙ ኢዛና) ከተባለ ወታደር ጋር በመሆን የሰላም ተጓዥ ነኝ ብሎ በመገናኛ ብዙሃን ሲታይ ነበር። አለማየሁ እና ኢዛና በየሃገሩ እየዞሩ ስለ አዲሱ ስርዓት መልካምነት ሲሰብኩ ከረሙ። ከዚያም አስመራ ድረስ ተልከው የሻእቢያውን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂን በወታደሩ ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።
አለማየሁ እና ኢዛና ለወያኔ በሰሩት ውለታ ሆላንድ ገብተው እንዲቀሩ ተደረገ። ይህም የተደረገበት ምክንያት በአውሮፓ የሚኖሩ ኢዮጵያውያንን ተቃዋሚ በመምሰልና በረቀቀ መንገድ እንዲያበጣብጡና እንዲሰልሉ ነው።
በሆላንድ ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ ለወያኔ ቡድን የስለላ ስራ መስራት ወንጀል ነው። አለማየሁ የሆላንድ ዜግነት ቢኖረው ኖሮ ቅጣቱ የከፋ ይሆን እንደነበር ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
የአለማየሁ መባረር በተሰማ ግዜ በሮተርዳም ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች የአቤቱታ ደብዳቤ በመጻፍ ፊርማ ማሰባሰብ ቢጀምሩም ሊሳካላቸው አልቻለም። የአቤቱታ ደብዳቤው ግለሰቡ እዚህ የተወለዱ ሁለት ለጆቹን እየመጣ እንዲጎበኝ ይፈቀድለት የሚል ነበር።
አለማየሁ ስንታየሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሆላንድ ተባረረ። ኢዛና ግን አሁን የተቃዋሚ ጭንብሉን አውልቆ በግልጽ ወያኔ መሆኑን መናገር ጀምሯል። ኢዛና የሆላንድ ዜግነት ቢኖረውም በሆላንድ ሃገር ስራ ሰርቶ አያውቅም። የቀንና ማታ ስራው በፓልቶክ ላይ ነው። ባለፈው ወር ኢትዮጵያ የተጓዙ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮችን እየመራ በቴሌቭዥን መግለጫ ሲሰጥ አይተነዋል። ይህ ትርኢት የወያኔ ኢንቨስተሮች በጨበጣ እንደሚንቀሳቀሱም ያሳየናል።

Tuesday, February 17, 2015

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የትግል ጥሪ አስተላለፈ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሁለተኛ ዙር የሠላማዊ ትግል ጥሪውን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተላለፈ፡፡ ትብብሩ የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ከተሞች ሊያደርገው አቅዶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በሳምንት አራዝሞ ለየካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ማስተላለፉንም አስታውቋል፡፡
ትብብሩ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ገዢው ፓርቲ የቱንም ያህል አሰቃቂና አረመኔያዊ የአፈና እርምጃዎች ቢወስድም የህዝብ ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ድረስ ህዝባዊ ትግሉን ማዳፈን እንጂ ማስቆም እንደማይችል ይልቁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተለያዩ የህዝብ እንቅስቃሴዎች መገንዘቡን ገልጹዋል፡፡ ትብብሩ ምርጫን በተመለከተ እንዳስታወቀው ኢህአዴግ ስለመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከቃላት ያለፈ እምነትም ሆነ ቁርጠኝነት የሌለው መሆኑን በዚህ የምርጫ ወቅት በተፎካካሪ ፓርቲዎች ላይ እየወሰደ ያለው ህገ-ወጥ እርምጃ ማሳያ ነው ብሏል፡፡
‹‹ለውጡ የሚመጣባቸው አምባገነኖች ድንገተኛ ከፍተኛ ፍርኃትና ሥጋት በማሳደሩ ህገ-መንግሥቱን በመጨፍለቅ በግልጽና በአደባባይ ህገ-ወጥ ውሳኔዎችንና እርምጃዎችን ለመውሰድ መገደዳቸው፣ ይህም የህዝቡን የለውጥ ፍላጎትና የትግል ተነሳሽነት በማሳደግ ህዝባዊውን ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገሩ የበለጠ ግልጽ ሆኗል›› ብሏል ትብብሩ፡፡
ትብብሩ አሁን ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ የአገራችንና ዜጓቿ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በሁለት አማራጮች ላይ የተንጠለጠለ ነው ያለው መግለጫው፣ አንድም ያለውን አምባገነናዊ ሥርዓት ተቀብሎ የጭቆና ቀንበር ተሸክሞ በከፋ ውርደት ሥር ሰጥ- ለጥ ብሎ መገዛት፣ አሊያም አምባገነንነትና ጭቆናን ‹‹በቃ›› በማለት በሕዝባዊ የተቀናጀ ሰላማዊ ትግል ለአገራችን ሉዓላዊነትና የዜግነት ክብራችንን ለማስመለስ በህገ መንግስታዊ መብታችን ተጠቅመን ትግላችንን እስከማይቀረው ለውጥ ድል ደጃፍ ድረስ በቆራጥነት መቀጠል ናቸው ብሏል፡፡
በዚህም ትብብሩ ህገ-መንግስታዊ መብትን በመጠቀም በህግና በሥርዓት ትግሉን ለመምራት መዘጋጀቱን በመግለጽ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የትግል ጥሪውን እንዲቀላቀሉት አሳስቧል፡፡ ስለሆነም ትብብሩ ‹‹ኢህአዴግነት ከዜግነት በላይ›› ለሆነባቸው የሥራ ዋስትናቸው፣ ዕድገትም ሆነ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በሙያቸው፣ በልምዳቸው፣ ክህሎታቸው፣ በመሳሰሉት ባልተመሰረተ መልኩ በደል እየደረሰባቸው ላሉ ሁሉ የትግል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
‹‹የህወኃት/ኢህአዴግ ተራ አባላትና ካድሬዎች፤ የፖለቲካ ልዩነት የተለያየ አመለካከትና ሀሳብ ማራመድ ጤናማ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ መገለጫ እንጂ እንደሚነገራችሁ ‹‹ጠላትነት›› ባለመሆኑ፣ ትግላችንም ለሠላማዊና ህጋዊ የሥልጣን ሽግግር እንጂ በናንተ ‹‹መቃብር›› ላይ አዲሱን ሥርዓት የማቆም፣ የነበረውን አጥፍቶ ከዜሮ የመጀመርና እናንተን የማጥፋት ዓላማ እንደሌለው ተረድታችሁ፣ ተቃዋሚዎች እንደናንተው ኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያና ህዝቧ የሚጨነቁ መሆናቸውን በመረዳት ተቃዋሚዎችን እንደ‹‹ ጠላት›› ከመመልከት አስተሳሰብ ራሳችሁን ነጻ እንድታወጡ›› ሲልም ትብብሩ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ወጣቶችና ሴቶች በተለይም የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች፣ መምህራንና ተማሪዎች በተለይም የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የእምነት ነጻነት መብት ጠያቂ የማኅበረሰብ አባላት፣ የመገናኛ ብዙሃን አባላት፣ የፍትህ አካላት፣ የዴሞክራቲክ ፓርቲዎች አባላት፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ሰላማዊ ታጋዮች፣ በውጪ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵዊያን/ዲያስፖራዎች እና ሌሎችም ጥሪው የተላለፈላቸው አካላት መሆናቸውን መግለጫው አትቷል፡፡
በመሆኑም፣ ‹‹በምናርገው አገራዊ፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል በማይቀረው የሥርዓት ለውጥ ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በአንድነትና በቆራጥነት እንድትሰለፉ፤ የካቲት 22/07 በየከተሞቹ በቦታውና በሰዓቱ እንድትገኙ ጥሪያችንን አበክረን እናቀርባለን›› ብሏል የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር፡፡

Ethiopia's Media War: Al Jazeera, The Stream

Ethiopia’s jailed Zone 9 bloggers are on trial this week for terrorism and treason, charges facing more than two dozen journalists, bloggers and publishers. To avoid arrest, 30 journalists fled the country in the past year. The government says they’re criminals, destabilising Ethiopia’s fragile democracy in the name of “press freedom.” Rights groups say they’re victims of repression.




Sunday, February 15, 2015

The 60th Birthday celebration of Andargachew Tesige in Oslo Norway | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

On february 14.2015 was a big day for DECSON celebrating our Hero Andargachew Tesige 60th birthday prepared by  (Democratic Change in Ethiopia Support Organization Norway)
As its known its has been almost 8 month since the brave hero and freedom fighter Andrgachew Tsgi has been kidnapped and arrested by the criminal regim TPLF.
Their was an invited gusts out of Norway who attend the celebration. People who love him and knows him were presented a speech about his patriotism and honest struggle. They called Him a true Ethiopian and the father of Ethiopians.
We Ethiopians can learn from Andargachew Tsige that freedom can not come without struggle and sacrifice.
Even though he is facing hard time in  Ethiopia he is remebered by the people who cares about him and will never stop pressing for his release until justice is served.
Hi is our hero and symbol of struggle that shows us commitment,devotion who cares for his motherland over his family. who never deserve to be in prison instead he deserves rewards for heroism.
- See more at: http://www.zehabesha.com/the-60th-birthday-celebration-of-andargachew-tesige-in-oslo-norway/#sthash.H3b0TL9H.dpuf

አባይ ጸሐዬ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የዛቱበት ድምጽ ተለቀቀ - "በአ.አ. ማስተር ፕላን ላይ ዳግም ጥያቄ ካነሱ ልክ እናስገባቸዋለን" አሉ - Zehabesha Amharic

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ም እመናንን ለሁለት በመክፈል የኢሕአዴግን የስልጣን ዘመን ያረዘሙት ሕወሓቱ አባይ ጸሃዬ ሰሞኑን በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ዛቱ:: ድምጻቸው ተቀርጾም በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ በኩል ለሕዝብ ይፋ ሆነ:: አባይ ጸሓዬ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ጉዳይ እንዲራዘም የተደረገው ሕዝቡ ባነሳው ተቃውሞ እንዳልሆነ ገልጸው በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸዋል::
የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንዳይሳካ የኦህዴድ ባለስልጣናትም ተባብረዋል ያሉት አባይ ጸሓዬ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ማስፋፊያ ዙሪያ ዳግመኛ ጥያቄ የሚያነሱትን ልክ እናስገባቸዋለን ብለዋል::
ከኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ የተገኘው ዜና የሚከተለው ነው::

አባይ ጸሐዬ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የዛቱበት ድምጽ ተለቀቀ - "በአ.አ. ማስተር ፕላን ላይ ዳግም ጥያቄ ካነሱ ልክ እናስገባቸዋለን" አሉ - Zehabesha Amharic